Logo

    በጉጂ በ30 የምርጫ ጣብያዎች ተቋርጦ የነበረዉ ምርጫ ዛሬ ተካሂዷል - ጁላይ 09, 2021

    amJuly 08, 2021
    What was the main topic of the podcast episode?
    Summarise the key points discussed in the episode?
    Were there any notable quotes or insights from the speakers?
    Which popular books were mentioned in this episode?
    Were there any points particularly controversial or thought-provoking discussed in the episode?
    Were any current events or trending topics addressed in the episode?

    About this Episode

    በአንድ የግል ተወዳዳሪ አቤቱታ ምክንያት ምርጫ ቦርድ ያቋረጠዉ የነጌሌ ምርጫ ዛሬ ተከናውኗአል። አቶ አማኑኤል ብርሃኑ የነገሌ የምርጫ ክልል አስተባባሪ የምርጫው ሂደት በ30 የምርጫ ጣብያዎች መከናወኑን ለአሜርካ ድምጽ ገልጸዋል። በምርጫዉ ከ150 በላይ የምርጫ ታዛቢዎች ተሳትፈዋል ብለዋል፣ ገልሞ ዳዊት ተጨማሪ አለዉ።

    Recent Episodes from ሳምንታዊ ዝግጅቶች - የአሜሪካ ድምፅ

    በኢትዮጵያ ላይ የተሰናዳው የአሜሪካ ሴኔት ረቂቅ ህግ - ማርች 31, 2022

    በኢትዮጵያ ላይ የተሰናዳው የአሜሪካ ሴኔት ረቂቅ ህግ - ማርች 31, 2022
    የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ 'በኢትዮጵያ ሰላምና ዲሞክራሲን ለማበረታታት' በሚል ርዕስ የቀረበውን S-3199 የተሰኘ ረቂቅ ተመልክቶ ማሻሻያዎች ካደረገ በኃላ አሳልፏል። ለመሆኑ ይህ ኮሚቴው ያሳለፈው ውሳኔ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ምን አንድምታ አለው? ረቂቅ ህጉ በቀጣይ የሚያልፍባቸው ሂደቶች ምን ይመስላሉ በሚለው ሀሳብ ዙሪያ በአሜሪካን ሀገር ሆነው ጉዳዩን የሚከታተሉ ተንታኞችን አነጋግረናል።

    በጉጂ በ30 የምርጫ ጣብያዎች ተቋርጦ የነበረዉ ምርጫ ዛሬ ተካሂዷል - ጁላይ 09, 2021

    በጉጂ በ30 የምርጫ ጣብያዎች ተቋርጦ የነበረዉ ምርጫ ዛሬ ተካሂዷል - ጁላይ 09, 2021
    በአንድ የግል ተወዳዳሪ አቤቱታ ምክንያት ምርጫ ቦርድ ያቋረጠዉ የነጌሌ ምርጫ ዛሬ ተከናውኗአል። አቶ አማኑኤል ብርሃኑ የነገሌ የምርጫ ክልል አስተባባሪ የምርጫው ሂደት በ30 የምርጫ ጣብያዎች መከናወኑን ለአሜርካ ድምጽ ገልጸዋል። በምርጫዉ ከ150 በላይ የምርጫ ታዛቢዎች ተሳትፈዋል ብለዋል፣ ገልሞ ዳዊት ተጨማሪ አለዉ።

    ሕወሓት ለድርድር ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች - ጁላይ 07, 2021

    ሕወሓት ለድርድር ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች - ጁላይ 07, 2021
    በሕወሐት የሚመራው የትግራይ ክልል መንግሥት፣ የተኩስ ማቆም ስምምነት ለማድረግ፣ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጠ። የክልሉ መንግስት ባወጣው መግለጫ፣ የኤርትራና የአመራ ክልል ሃይሎች ከክልሉ እንዲወጡ፣ ከክልሉ አለም አቀፍ በረራ ማካሄድን ጨምሮ፣ ሁሉም መገናኛ እንዲከፈቱ፣ ወደ ትግራይ ማንኛውም የፌደራል መንግስት፣ የጸጥታ አካል እንዳይገባ የሚሉ ቅድመ ሁኔታዎች ይገኙባቸዋል።(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

    ኢትዮጵያ ያስመረቀችው የሳተላይት መቀበያ ፋይዳው ምንድነው? - ሜይ 17, 2021

    ኢትዮጵያ ያስመረቀችው የሳተላይት መቀበያ ፋይዳው ምንድነው? - ሜይ 17, 2021
    የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ የብዝሃ ሳተላይት መረጃ መቀቢያ ጣቢያ ቅዳሜ ግንቦት 7፣ 2013 ዓ.ም አስመርቋል። የሳተላይት መረጃ መቀበያው በመስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው ሲሆን በቀጣይ ለሚደረጉ የሕዋ ሳይንስ ስራዎች ትልቅ መንደርደሪያ እንደሚሆን ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ በዚህ ዙሪያ ከኢትዮጵያ የስፔስ ማኅብረሰብ ስራአስኪያጅ ቤዛ ተስፋዬ ጋር አጠር ያለቆይታ አድርገናል፡፡

    በተቋሟ የሚሰሩ ሴቶችን የምታበቃው የተፈጥሮ የውበት መጠበቂያ አምራቿ ወጣት - ሜይ 08, 2021

    በተቋሟ የሚሰሩ ሴቶችን የምታበቃው የተፈጥሮ የውበት መጠበቂያ አምራቿ ወጣት - ሜይ 08, 2021
    ዮርዳኖስ ጉሽ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት የተማረች ሲሆን በተለያዩ የብሮድካስት እና የህትመት ሚዲያዎች ላይም ሰርታለች፡፡ በአሁን ሰዓት ደግሞ ኢትዮጵያን ስኪን ቢውቲ ሲክሪትስ የተሰኘ የተፈጥሮ የቁንጅና ግብዓቶች የሚያመርት ተቋም ከፍታለች፡፡ ዮርዳኖስ ባለፉት ሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ አብረዋት የሚሰሩ 12 ሰራተኞቿ የራሳቸውን ሱቅ ከፍተው እንዲወጡ በማድረግም ሴቶችን ማብቃት ላይ የራሷን ሚና እየተጫወተች ትገኛለች፡፡

    ኮቪድ-19 በሴቶች ሕይወት ላይ ያሳደረውን ጫና እና መፍትሄዎቹ - ቆይታ ከዮዲት አምሃ ጋር - ኤፕሪል 16, 2021

    ኮቪድ-19 በሴቶች ሕይወት ላይ ያሳደረውን ጫና እና መፍትሄዎቹ - ቆይታ ከዮዲት አምሃ ጋር - ኤፕሪል 16, 2021
    ወ/ሮ ዮዲት አምሃ ላለፉት 28 ዓመታት በዚህ በአሜሪካ ሃገር በሴቶች እና ብቸኛ ስደተኛ ህጻናት ላይ ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን በጾታ እኩልነት ዙሪያም ሰፊ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋሉ፡፡ ኮቪድ 19 በከፍተኛ ሁኔታ የአገልግሎት ዘርፉን ማጥቃቱና በዚህም የተነሳ በዘርፉ ውስጥ ያሉ እጅግ ብዙ ሴቶች መቸገራቸውን አንስተው የመፍትሄ አማራጮችን እና የተለያዩ ሴቶችን ያበቃሉ ያሏቸውን እድሎች ጠቁመዋል፡፡

    ከአንድ እስከ 8 ዓመት እድሜ ያሉ ሕጻናት የንባብ ባህል እንዲያዳብሩ መጽሃፍትን የማሰባሰብ እና ማዕከል መክፈት መርሃግብር - ማርች 25, 2021

    ከአንድ እስከ 8 ዓመት እድሜ ያሉ ሕጻናት የንባብ ባህል እንዲያዳብሩ መጽሃፍትን የማሰባሰብ እና ማዕከል መክፈት መርሃግብር - ማርች 25, 2021
    የነገ ተስፋ ሕጻናት ለአዲስ አበባ፤ የተሰኘው መርሃግብር በአ.አ አስተዳደር የህጻናት ቀዳማዊ ልጅነት መርሃግብር በኩል በ 10 ክፍለከተማዎች ከአንድ እስከ ስምንት ዓመት እድሜ ላሉ ሕጻናት የሚያገለግል የመጽሃፍት ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ እያዘጋጀ ይገኛል፡፡ ቢሮው በጎፍቃደኞች በዚህ የእድሜ ክልል ላሉ ሕጻናት የሚያገለግሉ መጽሃፍትን እንዲለግሱም ጥሪ አድርጓል፡፡ የመርሃግብሩ አስተባባሪ ዶ/ር ታቦር ገብረመድህን ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ አድርገው ነበር፡፡

    በየጊዜው የሚደረጉ የጽዋ፣ ጀማ እና የጸሎት መርሃግብሮች ሴቶችን ለማብቃት ምን ሚና አላቸው? - ማርች 20, 2021

    በየጊዜው የሚደረጉ የጽዋ፣ ጀማ እና የጸሎት መርሃግብሮች ሴቶችን ለማብቃት ምን ሚና አላቸው? - ማርች 20, 2021
    ከ160 ዓመት በፊት በጉራጌ ዞን እንደኖረች እና ለሴቶች መብት መከበር ትታገል እንደነበር በሚነገርላት በቃቄ ውርድወት ስም የተሰየመው መብቶች እና የዴሞክራሲ እድገት ማሕበር(CARD) የሚያዘጋጀው 'ውርድወት የምርምር መርሃግብር' ወይም ፌሎውሺፕ የመጀመሪያ ምርምር ውጤቱን ይፋ አድርጓል፡፡ ጥናቱ በየጊዜው በሴቶች የሚደረጉ የጽዋ ፣ ጀማ እና የጸሎት ቡድኖች በሴቷ ስነልቦናዊ እና ኢኮኖሚያ ሕይወት ዙሪያ ያላቸውን ሚና ላይ ያተኮረ ነው፡፡

    ግጭት በሕይወታቸው ላይ ያሳደረውን ስቃይ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ይናገራሉ - ማርች 13, 2021

    ግጭት በሕይወታቸው ላይ ያሳደረውን ስቃይ  ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ይናገራሉ - ማርች 13, 2021
    በሳምንቱ መግቢያ ላይ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ተከብሯል፡፡ በኢትዮጵያም በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍል ያሉ ግጭቶች ለሴቶች እና ህጻናት መፈናቀል፣ ለአካላዊ እና ስነልቦናዊ ጥቃት እንዳጋለጧቸው ይታወቃል፡፡ የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢዎች ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን በማስመልከት ኮቪድ 19 እና ግጭት በሴቶች ላይ ያሳደረውን ጫና ከተለያየ የሃገሪቱ ክፍል አሰባስበው የላኩትን ዘገባ ቆንጂት ታዬ እና ኤደን ገረመው እንደሚከተለው አጠናቅረውታል፡፡

    ለሴቷ ምርጫ ቅድሚያ የሚሰጠው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ምጣኔ እና የሚኖረው ጠቀሜታ - ማርች 10, 2021

    ለሴቷ ምርጫ ቅድሚያ የሚሰጠው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ምጣኔ እና የሚኖረው ጠቀሜታ - ማርች 10, 2021
    በአውሮፓዊያኑ 2021 ዓ.ም የተባበሩት መንግስታት ተቋማት የቤተሰብ ምጣኔ 2020(ሃያ ሃያ) የዓለም አቀፍ የትብብር እና ተነሳሽነት ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ ሪፖርቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ 67 ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ባላቸው ሃገራት ላይ የተሰራ ሲሆን ምንም እንኳን በድሃ ሃገራት ውስጥ ያለው የቤተሰብ ምጣኔ ተጠቃሚነት ቢጨምርም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ግን የቤተሰብ ምጣኔ እቅዱን በተገቢው መንገድ ለማስኬድ ትልቅ ስጋት እንደፈጠረ አመላክቷል፡፡
    Logo

    © 2024 Podcastworld. All rights reserved

    Stay up to date

    For any inquiries, please email us at hello@podcastworld.io