Logo

    ኮቪድ-19 እና ሌሎች ወረርሽኞች - የአሜሪካ ድምፅ

    የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡
    am50 Episodes

    People also ask

    What is the main theme of the podcast?
    Who are some of the popular guests the podcast?
    Were there any controversial topics discussed in the podcast?
    Were any current trending topics addressed in the podcast?
    What popular books were mentioned in the podcast?

    Episodes (50)

    ኢትዮጵያ ሦስተኛው የኮቪድ ማዕበል አስግቷል - ኦገስት 31, 2021

    ኢትዮጵያ ሦስተኛው የኮቪድ ማዕበል አስግቷል - ኦገስት 31, 2021
    በኢትዮጵያ የኮቪድ ወረርሽኝ ሦስተኛው ማዕበል እየጀመረ መሆኑን የሚጠቁሙ ምልክቶች እየታዩ ናቸው ሲል የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት አስታወቀ። ዴልታ የተሰኘው አዲሱ የኮቪድ-19 ዝርያ በሃገሪቱ መኖር አለመኖሩን በቅርቡ እንደሚያረጋግጥም ገለፀ። ወደ 22 ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በስድስት ወር ውስጥ የኮቪድ ክትባትን ለማዳረስም እየተሠራ ነው ተባለ።

    የአይምሮ ጤና ከአካላዊ ጤና እኩል ትኩረት ሊሰጠው ይገባል - ኦገስት 26, 2021

    የአይምሮ ጤና ከአካላዊ ጤና እኩል ትኩረት ሊሰጠው ይገባል - ኦገስት 26, 2021
    የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ሀገራት የአይምሮ ጤና ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። በሽታው በቀጥታ በአይምሮጤና ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት በተጨማሪ ወረርሽኙ በሀገራት ኢኮኖሚ ላይ ባደረሰው ተፅእኖ ምክንያት ለአይምሮ ጤና ይደረግ የነበረው የገንዘብ ድጎማ በመመናመኑም ቀድሞውንም ደካማ የነበረው የህክምና አቅርቦት መቀነስ ችግሩን እያባባሰው ነው።

    የባይደን አስተዳደር ሁሉንም አሜሪካዊያን ለማስከተብ አዲስ ዕቅድ አውጥቷል - ጁላይ 12, 2021

    የባይደን አስተዳደር ሁሉንም አሜሪካዊያን ለማስከተብ አዲስ ዕቅድ አውጥቷል - ጁላይ 12, 2021
    በዩናይትድ ስቴትስ አንድ ሶስተኛ የሚሆነው ሕዝብ በኮሮና ቫይረስ አማካኝነት የሚመጣው የኮቪድ 19 በሽታ መከላከያ ክትባትን አልወሰደም፡፡ በክትባቱ ዙሪያ ያለው የሃሳብ ልዩነትም ቫይረሱን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት እያከበደው ይገኛል፡፡

    በኮቪድ 19 ተጠቅተው ጽኑ ህሙማን ክፍል የገቡ አፍሪካዊያን የመሞት እድላቸው እጅግ ሰፊ ነው - የአፍሪካዊያን ጽኑ ህሙማን ጥናት - ጁን 12, 2021

    በኮቪድ 19 ተጠቅተው ጽኑ ህሙማን ክፍል የገቡ አፍሪካዊያን የመሞት እድላቸው እጅግ ሰፊ ነው - የአፍሪካዊያን ጽኑ ህሙማን ጥናት - ጁን 12, 2021
    በኮቪድ 19 የተጠቁ እና በጽኑ የታመሙ አፍሪካውያን በሌላው የዓለም ካሉ ታማሚዎች ጋር ሲንጻጸር የመሞት እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን የአፍሪካ የኮቪድ 19 ጽኑ ህሙማን ላይ የተደረገ ጥናት አመላከተ፡፡ ጥናቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአስር የአፍሪካ ሃገራቶች ተካሂዷል፡፡ ይሄ ጥናት በቅርቡ ዘ ላንሴት በተሰኘው የህክምና መጽሄት ላይ ታትሟል፡፡

    ዩናይትድ ስቴትስ እስከ ሰኔ ወር ማብቂያ ድረስ 80ሚሊየን ክትባቶችን እንደምትለግስ ቃል ገባች - ጁን 05, 2021

    ዩናይትድ ስቴትስ እስከ ሰኔ ወር ማብቂያ ድረስ 80ሚሊየን ክትባቶችን እንደምትለግስ ቃል ገባች - ጁን 05, 2021
    ከመጪው የአሜሪካ የነጻነት ቀን ጁላይ ፎር በፊት 70 በመቶ የሚሆኑ አሜሪካዊያን አዋቂዎች የኮቪድ 19 ክትባት እንዲወስዱ ፕሬዘዳንት ጆባይደን ለአንድ ወር የሚቆይ ማበረታቻ መርሃግብር ጀመሩ፡፡ በተጨማሪም አተዳደራቸው ሃሙስ ዕለት 25 ሚሊየን የሚሆን ክትባት በተባበሩት መንግስታት በኩል ለኮቫክስ እንደሚለግስ አስታውቋል፡፡ ይህም እስከ ሰኔ ማብቂያ ድረስ 80 ሚሊየን ክትባት ለመለገስ ቃል ከተገባው ውስጥ የመጀመሪያው ነው፡፡

    የኮቪድ-19 ክትባት በትግራይ ክልል - ሜይ 21, 2021

    የኮቪድ-19 ክትባት በትግራይ ክልል - ሜይ 21, 2021
    መቀሌ ከተማ ከባለፈው መጋቢት ወር መጨረሻ ጀምሮ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ካደረጉ ሰዎች 37 በመቶ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ገልጿል። ቢሮው በከተማው እስከ አሁን ለ23ሺህ ሰዎች የቫይረሱ ክትባት እንደተሰጠ አስታውቋል። ምርመራውና ክትባቱ በክልሉ ሌሎች ከተሞች ለማካሄድ ማቀዱ ነው የገለፀው።

    በአፍሪካ ልውጥ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች ወረርሽኝ ሊያገረሽ ይችላል - ሜይ 07, 2021

    በአፍሪካ ልውጥ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች ወረርሽኝ ሊያገረሽ ይችላል - ሜይ 07, 2021
    በአፍሪካ ለኮሮና ቫይረስ የሚሰጠው ህይወት አዳኝ ክትባት ስርጭት በጣም አነስተኛ በመሆኑና አዳዲስ የቫይረሱ ዝርያዎች በስፋት እየተሰራጩ መሆኑን ተከትሎ የአፍሪካ ሀገራት የአዲስ ልውጥ ቫይረስ ወረርሽኝ ያሰጋቸዋል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቋል።

    በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ክትባት የተከተቡ ሰዎች ምን ይላሉ? - ሜይ 04, 2021

    በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ክትባት የተከተቡ ሰዎች ምን ይላሉ? - ሜይ 04, 2021
    ኢትዮጵያ የካቲት 28 2013 ዓ.ም 2.2 የአስትራዜኒካ ክትባት በመጋቢት አጋማሽ ደግሞ 300,000 የሳይኖፋርም ክትባቶችን ያገኘች ሲሆን የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት መሰጠት ሂደትም ጀምራለች፡፡ በሃገሪቱ ያለው የክትባት አሰጣጥ ሂደት ምን ይመስላል? የኅብረተስቡስ ግንዛቤ ስትል ኤደን ገረመው በጤና ሚኒስቴር የሚኒስትር አማካሪ እና የብሔራዊ የክትባት አስተባባሪ የሆኑትን ዶ/ር ሙሉቀን ዮሃንስ፣ ክትባቱን የወሰዱ ሰዎችን አነጋግራ ተከታዩን አሰናድታለች፡፡

    በኮቪድ-19 እና በፖለቲካ አለመረጋጋት የተፈተኑት የኢትዮጵያ ሚዲያ - ሜይ 03, 2021

    በኮቪድ-19 እና በፖለቲካ አለመረጋጋት የተፈተኑት የኢትዮጵያ ሚዲያ - ሜይ 03, 2021
    በብዙ ፈተኛዎች ውስጥ የኖረው የኢትዮጵያ ሚዲያ አሁን ደግሞ ዓለምን ባጠቃው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። በተለይ ባለፈው አንድ አመት ውስጥ በማስታወቂያ እጥረት ምክንያት ገቢ መቀነስ፣ መረጃ የማግኘት ችግር፣ ባልታወቁ አካላት በጋዜጠኞች ላይ የሚደርስ ማስፈራራትና ጥቃት እንዲሁም የሚዲያዎች መዘጋት ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ተቋማት ትልቅ ፈተናዎች ነበሩ።

    "ቅንነት ትልቅ ዋጋ አለው" - ቬርሳቬል መላኩ - ሜይ 03, 2021

    "ቅንነት ትልቅ ዋጋ አለው" - ቬርሳቬል መላኩ - ሜይ 03, 2021
    የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በአነስተኛ የንግድ ዘርፎች ላይ የነበረው ጫና የበረታ ሲሆን ብዙዎችን ከገበያ ውጪ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ይህ ጫና ካረፈባቸው አነስተኛ የንግድ ተቋማት መሀከል በአሜሪካን ሀገር፣ ቨርጂንያ ግዛት የሚገኘው ዘመን የጉዞ ወኪል አንዱ ሲሆን የድርጅቱ ባለቤት ቬርሳቬል መላኩ ድርጅቷ ከስራ ውጪ የሆነበትን አንድ አመት በሰሜን አሜሪካ ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ ነፃ የማማከርና የመረጃ አገልግሎት በመስጠት ስታገለግል ቆይታለች።

    በኢትዮጵያ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ የሚገኘው ኮቪድ-19 - ኤፕሪል 27, 2021

    በኢትዮጵያ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ የሚገኘው ኮቪድ-19 - ኤፕሪል 27, 2021
    በኢትዮጵያበኮቪድ 19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን በበሽታው ምክንያት ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡና ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ቀጥሏል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በሀገሪቱ ውስጥ የፅኑ ህሙማን አልጋ፣ ኦክስጅንና ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያዎች እጥረት የተከሰተ ሲሆን የቫይረሱ ተጠቂዎች ህክምና ለማግኘት መቸገራቸውን የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የታማሚ ቤተሰቦች ተናግረዋል።

    የኮቪድ-19 ምርመራ በትግራይ ክልል - ኤፕሪል 16, 2021

    የኮቪድ-19 ምርመራ በትግራይ ክልል - ኤፕሪል 16, 2021
    በትግራይ ክልል ባለፉት አምስት ወራት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምርመራ አልተካሄደም ሲል የክልሉ ጤና ምርምር ተቋም አስታወቀ። ተቋሙ እንደገለፀው በክልል አሁን ባለው የፀጥታ ችግርና በጤና ተቋማት ላይ በደረሰው ጉዳት የኮቪድ-19 ምርመራ ለማካሄድ አዳጋች እንዳደረገው ገልጿል። በቅርብ ቀናት በመቀሌ ከተማ በሚገኙ የጤና ተቋማት የኮረና ምርመራ እየተጀመረ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል።

    ኮሮና በትምህርት ላይ የሚያሳድረው ጫና እንደቀጠለ ነው - ኤፕሪል 15, 2021

    ኮሮና በትምህርት ላይ የሚያሳድረው ጫና እንደቀጠለ ነው - ኤፕሪል 15, 2021
    በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለዘጠኝ ወራት ተዘግተው የቆዩት ትምህርት ቤቶች አሁን በፈረቃ ማስተማር ቢጀምሩም ከትምህርታቸው ርቀው የቆዩት ተማሪዎች ላይ ያሳደረው ጫና ግን እንደቀጠለ መሆኑን ተማሪዎች ይገልፃሉ። በወረርሽኙ ምክንያት የመተዳደሪያ ገቢያቸውን ያጡ ወላጆችም የልጆቻቸውን የትምህርት ወጪ ለመሸፈን በመቸገራቸው አንዳንድ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ሳይመለሱ ቀርተዋል።

    ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ - ኤፕሪል 13, 2021

    ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ - ኤፕሪል 13, 2021
    በኢትዮጵያ ህዝቡ ኮቪድ-19ን ለመከላከል የሚያደርገው ጥረት አናሳ ነው ሲል የጤና ሚኒስቴር ገለጸ። የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እንዳስታወቀው፣ ለአለፉት ስድስት ወራት ለተደረጉት የዳሰሳ ጥናቶች ኮቪድ-19ን ለመከላከል የሚደረጉ ጥረቶች ዝቅተኛ ናቸው። በተለይ ት/ቤቶች ላይ 79 በመቶው የነበረው ወደ 76 በመቶው መውረዱን ጥናቱ ያሳያል ሲሉ በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ-19 ምርምርና ጥናት ግብረ ኃይል አስተባባሪ ዶ/ር አበባየሁ ገበየሁ ተናግረዋል።

    የሀይማኖት አባቶች የፀረ-ኮቪድ 19 ክትባት ወሰዱ - ኤፕሪል 08, 2021

    የሀይማኖት አባቶች የፀረ-ኮቪድ 19 ክትባት ወሰዱ - ኤፕሪል 08, 2021
    በኢትዮጵያ የሀይማኖት አባቶች ዛሬ የኮቪድ-19 ክትባትን ወስደዋል። ኅብረተሰቡ የመከተብ ዕድል ሲያገኝ ክትባቱን እንደሚገባውም ያሳሰቡት የኃይማኖችት አባቶቹ፤ ሕዝቡ ራሱን ከኮሮናቫይረስ እንዲከላከልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

    ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በታንዛኒያ - ኤፕሪል 07, 2021

    ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በታንዛኒያ - ኤፕሪል 07, 2021
    ታንዛኒያ ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ትኩረት አለመሰጠቷ እንደሚያሳስባቸው እዚያ ለብዙ ዓመታት የኖሩ ትውልደ-ኢትዮጵያ ገልፀዋል። የኮቪድ-19 ክትባት የሚኖሩበት ሀገር ውስጥ እንደሌለም አመልክተዋል። ለኢትዮጵያዊያኑ ስጋት ምላሽ በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መልስ ሰጥቷል።

    ኮቪድ 19 የፈጠረው የስራ ጫና እና ኢትዮጵያዊያን ሃኪሞች እያሳለፉት ያለው ጊዜ - ኤፕሪል 01, 2021

    ኮቪድ 19 የፈጠረው የስራ ጫና እና ኢትዮጵያዊያን ሃኪሞች እያሳለፉት ያለው ጊዜ - ኤፕሪል 01, 2021
    ያለፈውን አንድ ዓመት ከኮቪድ 19 ጋር ሲታገሉ የከረሙት ኢትዮጵያዊያን ሃኪሞች ዘንድሮም ወረሽኙ በማገርሸቱ ከባድ የስራ ጫና ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በዓለም ዙሪያ ሃኪሞች በስራ ጫና ለሚመጣ ጭንቀት፣ ድብርት እና መዳከም ወይም በእንግሊዘኛው በርን አውት መጋለጣቸው እየተነገረ ነው፡፡ በተመሳሳይ ኢትዮጵያዊያን ሃኪሞችም ከፍተኛ ለሆነ ጭንቀት፣ አካላዊ እና መንፈሳዊ ድካም በመጋለጣቸው የተለያ ባህሪ ማዳበር፣ ማልቀስ እና ጭንቀት እንደ ታየባቸው ለአሜሪካ ድምጽ አጋርተዋል፡፡