Logo

    ጋቢና ቪኦኤ - የአሜሪካ ድምፅ

    የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡
    am50 Episodes

    People also ask

    What is the main theme of the podcast?
    Who are some of the popular guests the podcast?
    Were there any controversial topics discussed in the podcast?
    Were any current trending topics addressed in the podcast?
    What popular books were mentioned in the podcast?

    Episodes (50)

    የተሰናባቹ 2013 ዓ.ም ፈታኝ ሁነቶች እና የአዲሱ አመት ተስፋ - ሴፕቴምበር 10, 2021

    የተሰናባቹ 2013 ዓ.ም ፈታኝ ሁነቶች እና የአዲሱ አመት ተስፋ - ሴፕቴምበር 10, 2021
    ኢትዮጵያውያን እየተሰናበቱት ያለው 2013 ዓ.ም በብዙ ፈታኝ ሁነቶች የተሞላ ነበር። አመቱ ላለፉት አስር ወራት በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ጨምሮ፣ በርካታ ግጭቶች፣ ኮቪድ 19 ወረርሽኝ፣ የዋጋ ግሽበትና ተፈጥሮአዊ አደጋዎች የተስተናገዱበት ሆኖ አልፏል ። እነዚህን ተግዳሮቶች ምን ይመስሉ ነበር? በመጪው 2014 ዓመተ ምህረትስ ምን ይጠበቃል?

    ለተቸገሩ ህሙማን እና አስታማሚዎች ማረፊያ የሆነችው ሀኪም - ሴፕቴምበር 03, 2021

    ለተቸገሩ ህሙማን እና አስታማሚዎች ማረፊያ የሆነችው ሀኪም - ሴፕቴምበር 03, 2021
    አሜሪካ በየአመቱ ለአፍሪካ ወጣት መሪዎች በምታዘጋጀው የማንዴላ ፌሎውሺፕ በዚህ አመት ከኢትዮጵያ ከተመረጡት መሀከል ጎጆ የህሙማን መጠለያ ተቋምን የመሰረተችው ዶክተር ሰላሜነሽ ፅጌ አንዷ ናት። ተቋሙ ከኢትዮጵያ የገጠር ከተሞች ለተጨማሪ ህክምና አዲስ አበባ የሚመጡ፣ ማረፊያ በማጣትና ገንዘባቸውን ለህክምና በመጨረስ ለጎዳና ህይወት የሚዳረጉ ህሙማንን በጊዜያዊነት የሚያስጠልል ሲሆን ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ ከ81 ሺህ በላይ የሚሆኑ ህሙማን ረድቷል።

    ልጆችዎ ትምህርት ቤት መሄድ ቢጠሉ ምን ያደርጋሉ? - ሴፕቴምበር 03, 2021

    ልጆችዎ ትምህርት ቤት መሄድ ቢጠሉ ምን ያደርጋሉ? - ሴፕቴምበር 03, 2021
    ህፃናት የትምህርት መማሪያ ጊዜያቸው ደርሶ ወደ ትምህርት ቤት ሲገቡ ወይም ካደጉ በኃላ በህይወታቸው በሚደርሱ የተለያዩ ገጠመኞች ምክንያት ትምህርት ቤት መሄድን ሊፈሩና ሊጠሉ ይችላሉ። በተለይ ከፍ እያሉ ሲሄዱ ትምህርት ቤት ውስጥ ሊያጋጥማቸው የሚችል ዝቅተኛ የመሆን ስሜት፣ የአካባቢ መቀየር፣ በወላጅ መሀል የሚደርስ ፍቺ ወይም ሞት ልጆች ትምህርት ቤት መሄድን እንዲጠሉ ሊያደርጋቸው ይችላል። ይህ ሁኔታ ሲያጋጥም ልጆች ፍርሀታቸውን ማሸነፍ እንዲችሉ ምን ማድረግ ይቻላል?

    'ዓለምን በቀጣይ ከሚያሰጓት ወረሽኞች ለመከላከል የሚያጠናው ግሎባል ዋን ሄልዝ' ቆይታ ከፕሮፌሰር ወንድወሰን አበበ ጋር - ኦገስት 26, 2021

    'ዓለምን በቀጣይ ከሚያሰጓት ወረሽኞች ለመከላከል የሚያጠናው ግሎባል ዋን ሄልዝ' ቆይታ ከፕሮፌሰር ወንድወሰን አበበ ጋር - ኦገስት 26, 2021
    ግሎባል ዋን ሄልዝ ኢንሺየቲቭ ወይም አንድ የዓለም ጤና ተነሳሽነት በአሜሪካ ሃገር በሚገኘው በኦሃዮ ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት የተመሰረተ ሲሆን ዓላማውም ከአካባቢ፣ ከእንሣት እና ከሰዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸው እንደ ኮቪድ 19፣ ኢቦላ፣ የእብድ ውሻ በሽታ፣ በነፍሳት ፣ በውሃ፣ በዓየር..የሚመጡ በሽታዎችን በኢትዮጵያ፣ ኬኒያ፣ ዩጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ሜክሲኮ፣ ብራዚል እና ታይላንድ...እየተንቀሳቀሰ የሚያጠና ነው፡፡ ይሄ ተነሳሽነት ከተመሰረተ ዘንድሮ 10ኛ ዓመቱ ይዟል፡፡

    ከ500 በላይ ታዳጊዎችን ያሳተፈው የሕዋ ሳይንስ የክረምት ትምህርት ምን ምን ነገሮችን ይዟል? - ኦገስት 26, 2021

    ከ500 በላይ ታዳጊዎችን ያሳተፈው የሕዋ ሳይንስ የክረምት ትምህርት ምን ምን ነገሮችን ይዟል? - ኦገስት 26, 2021
    የኢትዮጵያ የሕዋ ሳይንስ ማኅበረሰብ ዘንድሮ ለየት ባለ ሁኔታ ልዩ መርሃግብር በመቅረጽ በአዲስ አበባ እና በአዳማ ከተማ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 550  ለሚሆኑ የአንደኛ፤ የሁለተኛ ደረጃ እና የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ልዩ የክረምት ስልጠና አዘጋጅቶ ስለሕዋ ሳይንስ ሲያስተምር ቆይቷል፡፡ የመርሃግብሩ ተሳታፊ የሆኑ ሁለት ታዳጊዎች እና በኢትዮጵያ የሕዋ ሳይንስ ማኅበረሰብ ውስጥ መርሃግብሮች አስተባባሪ የሆኑትን አቶ ብሩክ ተረፈን ከጋቢና ቪኦኤ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

    የአይምሮ ጤና ከአካላዊ ጤና እኩል ትኩረት ሊሰጠው ይገባል - ኦገስት 26, 2021

    የአይምሮ ጤና ከአካላዊ ጤና እኩል ትኩረት ሊሰጠው ይገባል - ኦገስት 26, 2021
    የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ሀገራት የአይምሮ ጤና ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። በሽታው በቀጥታ በአይምሮጤና ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት በተጨማሪ ወረርሽኙ በሀገራት ኢኮኖሚ ላይ ባደረሰው ተፅእኖ ምክንያት ለአይምሮ ጤና ይደረግ የነበረው የገንዘብ ድጎማ በመመናመኑም ቀድሞውንም ደካማ የነበረው የህክምና አቅርቦት መቀነስ ችግሩን እያባባሰው ነው።

    የላም ወተት የተዘጋጀ የጸጉር ቅቤን አሽጋ ለዓለም የምትሸጠው ኢትዮጵያዊት - ኦገስት 10, 2021

    የላም ወተት የተዘጋጀ የጸጉር ቅቤን አሽጋ ለዓለም የምትሸጠው ኢትዮጵያዊት - ኦገስት 10, 2021
    ወ/ሮ ገነት ስለሺ የፎቶግራፍ ባለሞያ ስትሆን ነዋሪነቷ በአሜሪካ ሃገር ነው፡፡ በዓመታት ከሃገር ውጪ ቆይታዋ ያጋጠማት የጸጉር መርገፍ፣ መጎዳት እና ተስማሚ የሆነ ምርት ማጣት ችግር 'ሹሩባ የጸጉር ቅቤ' የተሰኘ ከላም ወተት የተመረተ የጸጉር ቅቤ ማምረቻ ተቋም እንድትከፍት እና ለዘመናት የቆየው የኢትዮጵያዊያን ጸጉርን ቅቤ የመቀባት ባህል ከኢትዮጵያ ውጪም እንዲስፋፋ ማድረግ እንድትችል አድርጓታል፡፡

    የቲያትር 100ኛ ዓመት በጎንደር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሲዘከር - ጁላይ 31, 2021

    የቲያትር 100ኛ ዓመት በጎንደር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሲዘከር - ጁላይ 31, 2021
    በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የጎንደር ዩኒቨርስቲ የቲያትር ጥበባት ክፍል ዘመናዊ ቲያትር በኢትዮጵያ የተጀምረበትን መቶኛ ዓመት በማሰብ ለሁለት ቀናት የቆየ መርሃግብር አካሂዷል፡፡ መርሃግብሩን የወልቂጤ፣ ደብረማርቆስ እና የወሎ ዩኒቨርስቲ የቲያትር ጥበብ ክፍሎችም የተሳተፉ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ የዘመናዊ ቲያትር ጅማሮን አስታኮ በመላው ሃገሪቱ የቲያትር ጥበብ እንዲነቃቃ እና እንዲያድግ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ስለቲያትር ቡድን አባላትም በቦታው ተገኝተው ውይይቱን ተካፍለዋል፡፡

    ሴትን ማስተማር ማህበረሰብን ማስተማር ነው - ጁላይ 29, 2021

    ሴትን ማስተማር ማህበረሰብን ማስተማር ነው - ጁላይ 29, 2021
    ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ትምህርት ቤት የሚገቡ ሴት ህፃናት ቁጥር ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ ቢሄድም አሁንም ሴት ተማሪዎች በሚያጋጥሟቸው በርካታ ተግዳሮቶች ምክንያት ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ይገደዳሉ። CAMFED (ትምህርት ለሴቶች ዘመቻ) የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ግን ላለፉት 18 አመታት ለተማሪዎችና ወላጆች የኢኮኖሚ አቅም በመፍጠር፣ እንዲሁም በአህጉሪቱ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በማገዝ ከ4.8 ሚሊዮን በላይ ሴት ህፃናት በትምህርት ቤት እንዲቆዩ አድርጓል።

    "የፓርኪንሰን ችግር ሰፊ ቢሆንም ስራችንን ከአዲስ አበባ ውጪ እንዳናስፋፋ የበጀት ችግር አለብን" ክብራ ከበደ - ጁላይ 15, 2021

    "የፓርኪንሰን ችግር ሰፊ ቢሆንም ስራችንን ከአዲስ አበባ ውጪ እንዳናስፋፋ የበጀት ችግር አለብን" ክብራ ከበደ - ጁላይ 15, 2021
    የፓርኪንሰን ሕሙማን ድጋፍ ማኅበር በኢትዮጵያ ከተመሰረተ አስራ ሁለት ዓመት ይሆነዋል፡፡ የድርጅቱ መስራች ክብራ ከበደ ትሰኛለች፡፡ ማኅበሩ ከተመሰረተ ጀመሮ በበሽታው ዙሪያ ግንዛቤን ለመፍጠር የእግር ጉዞዎች፣ የውይይት ምሽቶች፣ የምክር አገልግሎቶች የሚሰጥ ሲሆን ለሕሙማኑም የምክር፣ የገንዘብ እና የሕክምና ድጋፍ እንዲያገኙ በማመቻቸት እየሰራ ይገኛል፡፡

    የምግብ ዋጋ ግሽበት ከቁጥጥር ውጪ እንዳይሆን ያሰጋል - ጁላይ 09, 2021

    የምግብ ዋጋ ግሽበት ከቁጥጥር ውጪ እንዳይሆን ያሰጋል - ጁላይ 09, 2021
    ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን የምግብ ዋጋ ንረት ለማረጋጋት መንግስት መሰረታዊ የምግብ ሸቀጦች በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ ማድረጉ በህብረተስቡ ዘንድ የሚታየውን የኑሮ ውድነት እንዳላቃለለ፣ የምግብ ዋጋም ከበፊቱ ይበልጥ እየጨመረ እንደሄደ ሸማቾች ይናገራሉ። ፍራንኮ ቫሉታ ብቻውን የዋጋ ንረቱን አያስተካክልም የሚሉት የምጣኔ ሀብት ተንታኞችም በኢኮኖሚውና በፓለቲካው ዙሪያ አስቸኳይ ማሻሻያዎች ካልተደረጉ ግሽበቱ መመለስ ወደማይቻልበት ደረጃ ሊደርስ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

    ወጣቱ የቴክኖሎጂ ፈጣሪ - ጁላይ 06, 2021

    ወጣቱ የቴክኖሎጂ ፈጣሪ - ጁላይ 06, 2021
    የሶስተኛ አመት ሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ ተማሪ የሆነው ናትናኤል ታምሩ የፈጠራ ችሎታውን ማሳደግ የጀመረው ገና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ ሲሆን ስማርት ሀውስ ወይም የውጪውን ሁኔታ በማስተዋል እራሱን የሚቆጣጠር ቤት እና የስልክ አጠቃቀምን የሚያቀል መተግበሪያዎችን በመስራት ሀገር አቀፍ ሽልማቶችን አግኝቷል። በዚህ ስራውና በትምህርቱ ባለው ውጤትም ካሊፎርኒያ ውስጥ የሚገኝ ዩንቨርስቲ ነፃ የትምህርት እድል ሰጥቶታል።

    በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ማየት የተሳነው ቦይ ስካውት - ጁን 24, 2021

    በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ማየት የተሳነው ቦይ ስካውት - ጁን 24, 2021
    የአዲስ አበባ ስካውት ማህበር በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን አይነስውር ስካውት ከዳግማዊ ሚኒሊክ አንደኛ ድረጃ ትምህርት ቤት ለስካውት ለቃለ መሃላ አብቅቷል።። ከተመሰረተ ከመቶ አመታት በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ስካውት ማህበር አባላት የሆኑ የተለያዩ የአካል ጉዳተኞች ያላቸው ስካውቶች ቢኖሩም ማየት የተሳነው አባል ግን ኖሮት እንደማያውቅ የማህበሩ ምክትል ኮሚሽነር ወልጊኛ ሁንዴሳ ነግረውናል።

    የአሜሪካ መንግስት ለልዩ ፍላጎት ትምህርት ብቻ በየአመቱ 13 ቢሊዮን ዶላር ያወጣል - ወይዘሮ አዜብ አታሮ - ጁን 24, 2021

    የአሜሪካ መንግስት ለልዩ ፍላጎት ትምህርት ብቻ በየአመቱ 13 ቢሊዮን ዶላር ያወጣል - ወይዘሮ አዜብ አታሮ - ጁን 24, 2021
    በአሜሪካን አገር ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ልጆች የሚያስተምሩ አካታች ትምህርት ቤቶች በስፋት ቢኖሩም ኢትዮጵያዊ ወላጆች በሚኖራቸው የግንዛቤ እጥረት ወይም የቅርብ ክትትል ማነስ ምክንያት ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆቻቸው የሚገባቸውን ድጋፍ ላያገኙ እንደሚችሉ በልዩ ፍላጎት ትምህርት ዙሪያ የሚሰሩ ባለሙያዎች ይገልፃሉ። እነዚህ ወላጆች ለልጆቻቸው ስኬት ምን ማድረግ አለባቸው፣ ከትምህርት ቤቶችስ ምን አይነት ድጋፍ ይጠበቃል?

    ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው የምርጫ ወቅት የሴቶች ጥቃት ምልከታና ውጤቱ - ጁን 24, 2021

    ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው የምርጫ ወቅት የሴቶች ጥቃት ምልከታና ውጤቱ - ጁን 24, 2021
    የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ ሴቶች ማኅበር (ኢውላ) በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጾታዊ ትንኮሳዎችን እና ጥቃቶችን ሲታዘብ ቆይቷል፡፡ በዛሬው ዕለትም በአዲስ አበባ የምርጫ ሂደቱ ቅድመ ምልከታው ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡