Logo

    ምጣኔ ኃብት - የአሜሪካ ድምፅ

    የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡
    am50 Episodes

    People also ask

    What is the main theme of the podcast?
    Who are some of the popular guests the podcast?
    Were there any controversial topics discussed in the podcast?
    Were any current trending topics addressed in the podcast?
    What popular books were mentioned in the podcast?

    Episodes (50)

    ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዕድገት ዕድል ድንጋጌ (አጎአ)አባል ሆና መቀጠል ይኖርባታልን? - ኦክቶበር 28, 2021

    ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዕድገት ዕድል ድንጋጌ (አጎአ)አባል ሆና መቀጠል ይኖርባታልን? - ኦክቶበር 28, 2021
    በጎረጎሳዊያኑ 2000 ዓመተምህረት የተፈረመው የአፍሪካ ዕድገት ዕድል ድንጋጌ (አጎአ) ዩናትይድ ስቴትስ እና አፍሪካዊያን ሀገራትን በንግድ ዘርፍ ያጣመረ ሰነድ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጦርነት እና ሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ደጋግሞ ስሟ የተነሳው ኢትዮጵያ ከዚህ የተጠቃሚነት ሰነድ ልትሰረዝ እንደምትችል ስጋት አይሏል። ሀብታሙ ስዩም ይሄ እንዳይሆን ዘመቻ ከጀመሩ ፣ በአንጻሩ ደግሞ እርምጃው እንዲወሰድ የሚፈልጉ ትውልደ -ኢትዮጵያዊያንን ሀሳብ በመቀጠል ያሰማናል ።

    የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት በአዲስ አበባ - ኦገስት 31, 2021

    የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት በአዲስ አበባ - ኦገስት 31, 2021
    የዋጋ እጅግ እያሻቀበ መምጣትና የኑሮው መወደድ የየዕለት ፈተና እየሆነባቸው መሆኑን አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ የአዲስ አበባ ተናግረዋል። በሀገሪቱ እየታየ ያለው የኑሮ ውድነት መንስዔዎች የኮቭድ 19 ወረርሽኝና ሀገሪቱ የገባችበት ጦርነት መሆናቸውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት የምጣኔ ኃብት ባለሙያ ዶክተር ብርሃኑ ደኑ ገልፀዋል። ቀውሱን ለመቆጣጠር መንግሥት የተለያዩ ምጣኔ ኃብታዊ የእርምት እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሆነ እየተገለፀ ነው።

    የምግብ ዋጋ ግሽበት ከቁጥጥር ውጪ እንዳይሆን ያሰጋል - ጁላይ 09, 2021

    የምግብ ዋጋ ግሽበት ከቁጥጥር ውጪ እንዳይሆን ያሰጋል - ጁላይ 09, 2021
    ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን የምግብ ዋጋ ንረት ለማረጋጋት መንግስት መሰረታዊ የምግብ ሸቀጦች በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ ማድረጉ በህብረተስቡ ዘንድ የሚታየውን የኑሮ ውድነት እንዳላቃለለ፣ የምግብ ዋጋም ከበፊቱ ይበልጥ እየጨመረ እንደሄደ ሸማቾች ይናገራሉ። ፍራንኮ ቫሉታ ብቻውን የዋጋ ንረቱን አያስተካክልም የሚሉት የምጣኔ ሀብት ተንታኞችም በኢኮኖሚውና በፓለቲካው ዙሪያ አስቸኳይ ማሻሻያዎች ካልተደረጉ ግሽበቱ መመለስ ወደማይቻልበት ደረጃ ሊደርስ ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

    ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች በቦሳሶ - ጁን 19, 2021

    ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች በቦሳሶ - ጁን 19, 2021
    በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በፑንትላንድ ሶማሌ ቦሳሶ በሚገኘው የዓለም አቀፍ የስደተኞች ተቋም IOM በኩል ለመመለስ መወሰናቸውን ተሰምቷል፡፡የአሜሪካ ድምጽ እነዚህን ወጣቶችና በኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የስደተኞች ተቋም IOM ውስጥ የስደተኞች መልሶ ማቋቋም ብሔራዊ መርሃግብር አባል የሆኑትን እከዳር ጤናዬን አነጋግሯል፡፡

    ኮቪድ-19 በሴቶች ሕይወት ላይ ያሳደረውን ጫና እና መፍትሄዎቹ - ቆይታ ከዮዲት አምሃ ጋር - ኤፕሪል 16, 2021

    ኮቪድ-19 በሴቶች ሕይወት ላይ ያሳደረውን ጫና እና መፍትሄዎቹ - ቆይታ ከዮዲት አምሃ ጋር - ኤፕሪል 16, 2021
    ወ/ሮ ዮዲት አምሃ ላለፉት 28 ዓመታት በዚህ በአሜሪካ ሃገር በሴቶች እና ብቸኛ ስደተኛ ህጻናት ላይ ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን በጾታ እኩልነት ዙሪያም ሰፊ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋሉ፡፡ ኮቪድ 19 በከፍተኛ ሁኔታ የአገልግሎት ዘርፉን ማጥቃቱና በዚህም የተነሳ በዘርፉ ውስጥ ያሉ እጅግ ብዙ ሴቶች መቸገራቸውን አንስተው የመፍትሄ አማራጮችን እና የተለያዩ ሴቶችን ያበቃሉ ያሏቸውን እድሎች ጠቁመዋል፡፡

    ከቀርክሃ እንጨት ካልሲ እና ምንጣፎች የምታመርተው ወጣት ይዲዲያ ዳምጠው - ኤፕሪል 01, 2021

    ከቀርክሃ እንጨት ካልሲ እና ምንጣፎች የምታመርተው ወጣት ይዲዲያ ዳምጠው - ኤፕሪል 01, 2021
    ይዲዲያ ዳምጠው ወጣት ስራ ፈጣሪ ስትሆን አክሊል የተሰኘ ተቋም መስራች ናት፡፡ ከተመሰረተ ሁለት ዓመት እድሜ ያለው አክሊል በዋናነት በአካባቢ ጥበቃ ላይ ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ለማምጣት የሚጥር ተቋም ሲሆን ከቀርክሃ እንጨት ክር በማምረት የመጀመሪያ ምርቱ የሆነው ሳባ ካልሲ በማምረት ስራውን ጀምሯል፡፡ ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥም ልዩ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ንድፍ የያዙ ምንጣፎች እና ብርድልብሶችን ከቀርክሃ እያመረተ ይገኛል፡፡

    ከአንድ እስከ 8 ዓመት እድሜ ያሉ ሕጻናት የንባብ ባህል እንዲያዳብሩ መጽሃፍትን የማሰባሰብ እና ማዕከል መክፈት መርሃግብር - ማርች 25, 2021

    ከአንድ እስከ 8 ዓመት እድሜ ያሉ ሕጻናት የንባብ ባህል እንዲያዳብሩ መጽሃፍትን የማሰባሰብ እና ማዕከል መክፈት መርሃግብር - ማርች 25, 2021
    የነገ ተስፋ ሕጻናት ለአዲስ አበባ፤ የተሰኘው መርሃግብር በአ.አ አስተዳደር የህጻናት ቀዳማዊ ልጅነት መርሃግብር በኩል በ 10 ክፍለከተማዎች ከአንድ እስከ ስምንት ዓመት እድሜ ላሉ ሕጻናት የሚያገለግል የመጽሃፍት ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ እያዘጋጀ ይገኛል፡፡ ቢሮው በጎፍቃደኞች በዚህ የእድሜ ክልል ላሉ ሕጻናት የሚያገለግሉ መጽሃፍትን እንዲለግሱም ጥሪ አድርጓል፡፡ የመርሃግብሩ አስተባባሪ ዶ/ር ታቦር ገብረመድህን ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ አድርገው ነበር፡፡

    ታዳጊ እናቶች እና ልጆቻቸውን ከጎዳና ላይ አንስቶ እራሳቸውን እንዲችሉ የሚረዳው መሰረት በጎ አድራጎት - ማርች 25, 2021

    ታዳጊ እናቶች እና ልጆቻቸውን ከጎዳና ላይ አንስቶ እራሳቸውን እንዲችሉ የሚረዳው መሰረት በጎ አድራጎት - ማርች 25, 2021
    ገና በለጋ እድሜዋ የቤተሰቧን ሕይወት ለማሻሻል ስትል ወደ ትዳር የገባቸው ወ/ሮ መሰረት አዛገ በልጅነቷ የልጅ እናት ብትሆንም ኑሮን ታግላ እራሷን አብቅታለች፡፡ ነገር ግን በለጋ እድሜ የልጅ እናት መሆን የሚያመጣውን ችግር ለመቅረፍ በጎዳና ላይ የወደቁ እናቶችን በመሰብሰብ እና መጠለያ በመስጠት የተሃድሶ መርሃግብር እንዲያገኙና በኋላም ቤት ተከራይተው እራሳቸውን ችለው እንዲወጡ ለመርዳት በመሰረት በጎ አድራጎት ድርጅት በኩል እየጣረች ነው፡፡

    ጥቅሙ ሲያበቃ አትክልት ሆኖ የሚበቅለው ቦርሳ መስራች - ማርች 25, 2021

    ጥቅሙ ሲያበቃ አትክልት ሆኖ የሚበቅለው ቦርሳ መስራች - ማርች 25, 2021
    ረድኤት ታደሰ ተጠቅመው ሲጨርሱት ለም መሬት ላይ አትክልት ሆኖ መብቀል የሚችል የወረቀት ቦርሳ ለገበያ አብቅታለች፡፡ አሁን ላይ 'ፕላንተብል ባግስ' ስትል የሰየመችው የሚበቅል ቦርሳ በትንሽ መጠን ብቻ እየተመረተ ሲሆን ስራውን ለማስፋትም በብሉሙን የስራ ፈጣሪዎች ውድድር ላይ ገብታ ለመጨረሻው ዙር ካለፉት መሃከል ሆናለች፡፡

    "ወጣቶች ዩኒቨርስቲ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ ስለ ስራ ማሰብ መጀመር አለባቸው" አቶ ኤፍሬም በቀለ - ማርች 11, 2021

    "ወጣቶች ዩኒቨርስቲ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ ስለ ስራ ማሰብ መጀመር አለባቸው" አቶ ኤፍሬም በቀለ - ማርች 11, 2021
    ከከፍተኛ የትምህርት እና የሙያ ተቋማት እየተመረቁ የሚወጡ እጅግ ብዙ ወጣቶች በስራ ገበያው ላይ ተመጣጣኝ ስራ ሲያገኙ አይታይም፡፡ በዚም ምክንያት የተማሩ ወጣቶች በስራ ፍለጋ ከወራት እስከ ዓመት ሲጉላሉ ይስተዋላል፡፡ በአንጻሩ ቀጣሪዎችም ተወዳዳሪ የሆኑ ወጣቶች በበቂ ሁኔታ ገበያው ላይ እንደሌሉ ሲያነሱ ይሰማል፡፡ የስነልቦና ባለሞያ እና የስራ ቅጥር አማካሪ የሆኑት አቶ ኤፍሬም በቀለ ወጣቶች ስለ ስራ ማቀድ ያለባቸው ሲመረቁ ሳይሆን ገና ትምህርት ሲጀመሩ ነው ይላሉ፡፡

    ለሴቷ ምርጫ ቅድሚያ የሚሰጠው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ምጣኔ እና የሚኖረው ጠቀሜታ - ማርች 10, 2021

    ለሴቷ ምርጫ ቅድሚያ የሚሰጠው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ምጣኔ እና የሚኖረው ጠቀሜታ - ማርች 10, 2021
    በአውሮፓዊያኑ 2021 ዓ.ም የተባበሩት መንግስታት ተቋማት የቤተሰብ ምጣኔ 2020(ሃያ ሃያ) የዓለም አቀፍ የትብብር እና ተነሳሽነት ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ ሪፖርቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ 67 ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ባላቸው ሃገራት ላይ የተሰራ ሲሆን ምንም እንኳን በድሃ ሃገራት ውስጥ ያለው የቤተሰብ ምጣኔ ተጠቃሚነት ቢጨምርም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ግን የቤተሰብ ምጣኔ እቅዱን በተገቢው መንገድ ለማስኬድ ትልቅ ስጋት እንደፈጠረ አመላክቷል፡፡

    በስራ ቦታ እድገት እና የሴቶችን ፈተና ያካተተው የሕይወቴ ቅኝት - ማርች 08, 2021

    በስራ ቦታ እድገት እና የሴቶችን ፈተና ያካተተው የሕይወቴ ቅኝት - ማርች 08, 2021
    ፍጹም አጥናፈወርቅ ኪዳነማሪያም የጽኑ ሴቶች ማህበር አባል እና የሴቶች መብትን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ሃሳቧን በግልጽ በመናገር እና ሴቶችን በማስተባበር ትታወቃለች፡:በቅርቡም የሕይወቴ ቅኝት የተሰኘ እና በእውነተኛ የግል የሕይወት ተሞክሮዎቿ እና አጋጣሚዎች ዙሪያ ያተኮረ መጽሃፍ ለንባብ አብቅታለች፡፡

    ኢትዮጵያ ውስጥ ወጣቶች የስራ ፈጠራ ሃሳባቸውን መሸጥ ይችሉ ይሆን? - ማርች 03, 2021

    ኢትዮጵያ ውስጥ ወጣቶች የስራ ፈጠራ ሃሳባቸውን መሸጥ ይችሉ ይሆን? - ማርች 03, 2021
    ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የተማረ ወጣት ሃይል እየተፈጠረ መሆኑን ተከትሎ ብዙዎች የራሳቸው የስራ ፈጠራ ሃሳብ እያመንጩ ይገኛሉ፡፡ ይሁንና ብዙዎቹ የስራ ፈጠራቸውን ለመሞከርም ሆነ ወደ ተግባር ለማምጣት የመነሻ ወረት እጥረትና በንግድ ክህሎት ማነስ ምክንያት ህልማቸውን ማሳካት ሲያቅታቸው ይታያል፡፡ ይህን በተመለከተ  የአይስ አዲስ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ማርቆስ ለማን ኤደን ገረመው አነጋግራዋለች፡፡

    በኢትዮጵያ የተመረቱ የተፈጥሮ ሽቶዎችን ለገበያ ያበቁት ወጣቶች ጉዞ - ፌብሩወሪ 23, 2021

    በኢትዮጵያ የተመረቱ የተፈጥሮ ሽቶዎችን ለገበያ ያበቁት ወጣቶች ጉዞ - ፌብሩወሪ 23, 2021
    በኤዶም በቀለ እና ሰናይት ዳንኤል ሉሲ ፍራግራንስ አትዮጵያዊ የሆነ መዓዛ ያለው የሽቶ ማምረቻ ድርጅትን ስራ ካስጀምሩ ሶስት ወራት ተቆጠሩ፡፡ ከዩኒቨርስቲ ከተመረቁ አራት ዓመታት ያስቆጠሩት ሁለቱ ጓደኛሞች ከተፈጥሮ ግብዓቶች የተመረቱ ሃይላንደር እና ኢቮልቭ የተሰኙ የወንድ እና የሴት ሽቶዎችን ለገበያ አብቅተዋል፡፡