Logo
    Search

    የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ - 2020 - የአሜሪካ ድምፅ

    የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡
    amየአሜሪካ ድምፅ34 Episodes

    Episodes (34)

    የዩናይትድ ስቴትስ የመጨረሻው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ክርክር ዛሬ ይካሄዳል - ኦክቶበር 22, 2020

    የዩናይትድ ስቴትስ የመጨረሻው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ክርክር ዛሬ ይካሄዳል - ኦክቶበር 22, 2020
    የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ እና የዲሞክራቲክ ፓርቲው ተፎካካሪያቸው ጆ ባይደን ዛሬ ማታ ክርክር ያካሂዳሉ። ፕሬዚዳንታዊ ምርጫው እአአ ህዳር 3ቀን የሚካሄድ ሲሆን ይህ የዛሬው የመጨረሻው ክርክራቸው ይሆናል። የቪኦኤዋ ካሮላይን ፕረሱቲ ከቴኒሲ ናሽቪል ከተማ ያጠናቀረችውን ዘገባ ይዘናል።

    ትራምፕና ባይደን ከመራጮች ጋር ለጥያቄና መልስ ተገናኙ - ኦክቶበር 17, 2020

    ትራምፕና ባይደን ከመራጮች ጋር ለጥያቄና መልስ ተገናኙ - ኦክቶበር 17, 2020
    የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና ተፎካካሪያቸው የቀድሞ ም/ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከመራጮች የሚነሱ ጥቃቄዎችን በቀጥታ በትናንትናው እለት፣ የአዳራሽ ውስጥ ውይይት አካሂደዋል፡፡

    የምክትል ፕሬዚዳንትነት ተፎካካሪዎች ክርክር - ኦክቶበር 08, 2020

    የምክትል ፕሬዚዳንትነት ተፎካካሪዎች ክርክር - ኦክቶበር 08, 2020
    የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ እና የዴሞክራቲክ ፓርቲው ዕጩ የካሊፎርኒያዋ ሴኔተር ካመላ ሃሪስ ትናንት ረቡዕ ምሽት ዩታ ግዛት ሶልት ሌክ ሲቲ ውስጥ ክርክር አካሂደዋል።

    የደጋፊና ተቃዋሚዎች ሁከትና ቀጣዩ ምርጫ - ሴፕቴምበር 01, 2020

    የደጋፊና ተቃዋሚዎች ሁከትና ቀጣዩ ምርጫ - ሴፕቴምበር 01, 2020
    "የጥቁር ሰው ህይወት ዋጋ አለው" በሚሉት ተቃዋሚዎችና፣ በፕሬዚዳንት ትረምፕ ደጋፊ በሆኑ ነጮች መካከል፣ የተከሰተውን የከረረ ግጭት ተከትሎ ፣ የዘር ፖለቲካው የቀሰቀሰው ውጥረት በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ ቀዳሚው መናጋገሪያ ሆኗል፡፡

    ሁለተኛው የሪፖብሊካን ጠቅላላ ጉባኤ ውሎ - ኦገስት 26, 2020

    ሁለተኛው የሪፖብሊካን ጠቅላላ ጉባኤ ውሎ - ኦገስት 26, 2020
    ለአራት ቀናት በመካሄድ ላይ በሚገኘው የሪፖብሊካን ጠቅላላ ጉባኤ ሁለተኛው ቀን ላይ፣ ቀዳማዊት እመቤት ሜለኒያ ትረምፕ መራጮች ፕሬዚዳንት ትረምፕን ለምን በድጋሚ መምረጥ እንዳለባቸው ምክንያቶቻቸውን አስረድተዋል፡፡

    ከማላ ኸሪስ እና ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ - ኦገስት 22, 2020

    ከማላ ኸሪስ እና ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ - ኦገስት 22, 2020
    ከማላ ኸሪስ በቁጥር አንስተኛ ከሆነው ማኅበረሰብ የመጡ የትልቅ ፓርቲ ዕጩ ሴት እንደመሆናቸው፣ ከነጭ ውጭ ያለውን ባለቀለም የማኅበረሰብ ክፍል አነቃቅተው ያንቀሳቅሱታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይሁን እንጂ ከጆ ባይደን ጋር የተሰለፉት ኸሪስ ራሳቸው፣ ትልቅ ዕድል ብቻ ሳይሆን ብርቱ ፈተናም ይጠብቃቸዋል፡፡ የቪኦኤ ዘጋቢ ፓት ሲ ውድክስዋራ ከዌልምንግተን ደለዌር የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅራለች፡፡

    ከማላ ኸሪስ የምክትል ፕሬዚዳንትነት ዕጩነቱን ተቀበሉ - ኦገስት 20, 2020

    ከማላ ኸሪስ የምክትል ፕሬዚዳንትነት ዕጩነቱን ተቀበሉ - ኦገስት 20, 2020
    ትናንት ረቡዕ ለሦስተኛ ቀን በተካሄደው የዲሞክራቶች ጠቅላላ ጉባኤ ምሽት የካሊፎርኒያዋ ሰኔተር ከሚላ ኸሪስ የዕጩ ፕሬዘዳናት ጆ ባይደን አጋር ሆነው የተሰየሙበትን የምክትል ፕሬዚዳንትነት ዕጩነት ተቀብለዋል፡፡ በምሽቱ ተናጋሪዎች ከተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች መካከልም በየሰው እጅ ባለው ጠመንጃና ሽጉጥ የሚደርሰው ጥቃት የአየር ጠባይ ለውጥ እና ኮቪድ-19 ዋነኞቹ ነበሩ፡፡

    የመጀመሪያዋ ጥቁር አሜሪካዊት ዕጩ ምክትል ፕሬዚዳንት - ኦገስት 12, 2020

    የመጀመሪያዋ ጥቁር አሜሪካዊት ዕጩ ምክትል ፕሬዚዳንት - ኦገስት 12, 2020
    በመጭው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የዴሞክራቲክ ፓርቲው “ዕጩ ይሆናሉ” ተብለው የሚጠበቁት የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ቢመረጡ ምክትላቸው እንዲሆኑ ሴኔተር ካምላ ሃሪስን በይፋ አጭተዋል። አብረዋቸው እንዲወዳደሩም መርጠዋቸዋል።

    የጥቅምቱ የአሜሪካ ምርጫና ድምጽን በፖስታ ስለመላክ - ኦገስት 07, 2020

    የጥቅምቱ የአሜሪካ ምርጫና ድምጽን በፖስታ ስለመላክ - ኦገስት 07, 2020
    እየተስፋፋ ባለፈው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ በተወሰኑ የዩናይትድ ስቴት ክፍለ ግዛቶች የሚገኙ ሰዎች በመጭው የጥቅምት ወር ምርጫ ጣቢያዎች በአካል ተገኝተው ከመምረጥ ይልቅ ድምጻቸውን በፖስታ መስደድ ይፈልጋሉ፡፡

    የትራምፕ የፌደራል ኃይል ስምሪትና የከንቲባዎች ተቃውሞ - ጁላይ 23, 2020

    የትራምፕ የፌደራል ኃይል ስምሪትና የከንቲባዎች ተቃውሞ - ጁላይ 23, 2020
    የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ወንጀልና ህገወጥነት ሰፍኖባቸው ጨርሶ ከቁጥጥር ውጭ ሆነዋል ብለው ወደጠሯቸው ወደ ቺካጎና ዴሞክራት ከንቲባዎች ወደሚያስተዳደሯቸው ሌሎች ከተሞች የፌደራል ኃይሎችን የማሰማራት እቅዶቻቸውን ገፍተውበታል፡፡