Logo
    Search

    የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ - 2020 - የአሜሪካ ድምፅ

    የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡
    amየአሜሪካ ድምፅ34 Episodes

    Episodes (34)

    በጆርጂያው የምርጫ ውጤት የኢትዮጵውያንና ኤርትራውያን ድርሻ ምን ነበር? - ጃንዩወሪ 28, 2021

    በጆርጂያው የምርጫ ውጤት የኢትዮጵውያንና  ኤርትራውያን ድርሻ ምን ነበር? - ጃንዩወሪ 28, 2021
    በቅርቡ በጆርጅያ ክፍለ ግዛት የተደረገው የምክር ቤት እንደራሴዎች ምርጫ የመላው ዩናትድ ስቴትስን ትኩረ ስቦ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በዚህም ምርጫ የዴሞክራቲክ ፓርቲ እጩዎች የሆኑት ራፋኤል ዎርኖክ እና ጆን ኦሰፍ የተባሉት አሸንፈዋል፡፡

    ባይደን እገዳውን በማንሳታቸው ናይጄሪያውያን ተደስተዋል - ጃንዩወሪ 26, 2021

    ባይደን እገዳውን በማንሳታቸው ናይጄሪያውያን ተደስተዋል - ጃንዩወሪ 26, 2021
    ናይጄሪያውያን፣ ፕሬዚዳንት ባይደን፣ በፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው የመጀመሪያው ቀን፣ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስልምና እምነት ተከታዮች በሚበዙባቸው አገሮችና በአንዳንድ አፍሪካ አገሮች ላይ ጥለውት የነበረውን እገዳ በማንሳታቸው ተስፋቸው ማንሰራራቱን ተናግረዋል፡፡

    ከቀድሙት ልዩ የሆነው የ46ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት በዓለ ሲመት - ጃንዩወሪ 20, 2021

    ከቀድሙት ልዩ የሆነው የ46ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት በዓለ ሲመት - ጃንዩወሪ 20, 2021
    "የአሜሪካ ፕሬዘዳንታዊ በዓለ ሲመት ሰላማዊ የሆነ የስልጣን ሽግግር ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ የአሜሪካ ድምጹ ስቲቭ ሬዲስች የዩናይትድ ስቴትስ 46ኛው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን በዓለ ሲመት ከቀደሙት በምን እንደሚለይ ያደረሰንን ዘገባ ኤደን ገረመው አጠናቅራዋለች፡፡"

    ለባይደን ፕሬዚዳንታዊ በዓለ ሲመት ጥበቃው ተጠናክሯል - ጃንዩወሪ 13, 2021

    ለባይደን ፕሬዚዳንታዊ በዓለ ሲመት ጥበቃው ተጠናክሯል - ጃንዩወሪ 13, 2021
    በሚቀጥለው ሳምንት እኤአ ጥር 20 የሚደረገውን የተመራጩን ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዓለ ሲመት አስመልክቶ፣ ህግ አስከባሪዎችና በዋሽንግተን ዲሲ ዙሪያ ያሉ ባለሥልጣናት፣ የጸጥታ ጥበቃውን ከወዲሁ ለማጠናከር እስከ ዛሬ ታይቶ የማይታወቅ የደህንነት እምርጃዎችን ተግባራዊ እያደረጉ ነው፡፡

    በአሜሪካ ምክርቤት ለደረሰው ሁከት የአለም መሪዎች አስተያየት - ጃንዩወሪ 08, 2021

    በአሜሪካ ምክርቤት ለደረሰው ሁከት የአለም መሪዎች አስተያየት - ጃንዩወሪ 08, 2021
    እሮብ እለት ዋሽንግተን ዲሲ በተፈፀመውና ቢያንስ ለአራት ሰዎች መሞትና ለበርካቶች መታሰር ምክንያት በሆነው ሁከት የአለም መሪዎች ድንጋጤያቸውን እየገለፁ ነው። ሁከቱ የተፈጠረው የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ህዳር ወር ላይ በዩናይትድ ስቴትስ በተካሄደው ምርጫ ያሸነፉትን ጆ ባይደንን ተቃውመው ወደ ምክር ቤቱ ባመሩበት ወቅት ነው። የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድቤቶች ትራምፕ ምርጫ ተጭበርብሯል ሲሉ ያቀረቡትን አቤቱታ በተደጋጋሚ ውድቅ ማድረጋቸው ይታወቃል።

    የፕሬዚዳንት ትረምፕ ደጋፊዎች ድርጊት እና በዓለም ዙሪያ የተፈጠረው ስሜት - ጃንዩወሪ 07, 2021

    የፕሬዚዳንት ትረምፕ ደጋፊዎች ድርጊት እና በዓለም ዙሪያ የተፈጠረው ስሜት - ጃንዩወሪ 07, 2021
    የተሰናባቹ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ደጋፊዎች ትናንት የሀገሪቱ ምክር ቤት የሚገኝበትን ካፒቶል ህንጻ ላይ ያደረጉት ወረራ በዓለም ዙሪያ ድንጋጤ ኃዘን እና ምጸት የተደባለቀበት ምላሽ አስከትሏል።

    በአሜሪካ ጆርጂያ የሴነት ተወካዮች ምርጫና ትውልደ ኢትዮጵያውያን - ዲሴምበር 24, 2020

    በአሜሪካ ጆርጂያ የሴነት ተወካዮች ምርጫና ትውልደ ኢትዮጵያውያን - ዲሴምበር 24, 2020
    በቅርቡ ከተጠናቀቀው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጋር የህዝብ ተወካዮችና እንደራሴዎች ምርጫም አብሮ ሲካሄድ መቆየቱን ይታወቃል፡፡ በተለይም ሪፐብሊካን የሚቆጣጠሩትን የሴኔት ምክር ቤት ውጤት በመቀየር አብላጫውን ወንበር ሊያገኙ ይችላሉ የተባሉት የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባላት ሳያሸንፉ ቀርተዋል፡፡

    የባይደን ማሳሰቢያ - ኖቬምበር 20, 2020

    የባይደን ማሳሰቢያ - ኖቬምበር 20, 2020
    ተሰናባቹ የትረምፕ አስተዳደር “የሽግግሩን ሂደት ማስተጓጎሉን ካላቆመ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ኮቪድ-19ን ለመቆጣጠር የሚከናወነውን የዕቅድ ሥራ በሣምንታትና በወራት ሊያጓትተው ይችላል” ሲሉ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስጠንቅቀዋል።

    የትራምፕና ባይደን ርክክብ ሲጠበቅ ወረርሽኙ እየከፋ ነው - ኖቬምበር 17, 2020

    የትራምፕና ባይደን ርክክብ ሲጠበቅ ወረርሽኙ እየከፋ ነው - ኖቬምበር 17, 2020
    በዩናይትድ ስቴትስ የኮሮናቫይረስ ስርጭት እየተስፋፋ ባለበት በዚህ ወቅት፣ የ2020 ምርጫ አሸናፊ እንደሆኑ የተነገረላቸው የቀድሞ ም/ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ አገሪቱን ፈጥኖ ለመርዳት እንዲችሉ፣ የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር የርክክቡን ሂደት በዚህ ሳምንት እንዲጀምሩ እየጠየቁ መሆናቸውን የቪኦኤ ዘጋቢ ሚሼል ኩዪን ዘግባለች፡፡

    የባይደን አስተዳደር ታሪካዊ ፈተናዎች ይገጥሙታል - ኖቬምበር 11, 2020

    የባይደን አስተዳደር ታሪካዊ ፈተናዎች ይገጥሙታል - ኖቬምበር 11, 2020
    ብርቱ ፉክክር የታየበትን ምርጫ ካሸነፉ በኋላ፣ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ሙሉ ትኩረታቸውን፣ ክፉኛ ወደ ተከፋፈለችው፣ በወረርሽኝ ወደ ተመታችውና፣ ኢኮኖሚዋ እየተንገታገተ ወደምትገኘው አገራቸው በማዞር እንዴት አድርገው እንደሚያስተዳደሯት መላ መምታት ጀምረዋል፡፡

    ትረምፕ ውጤቱን ሲሞግቱ ባይደን የሽግግር ሥራ ጀምረዋል - ኖቬምበር 10, 2020

    ትረምፕ ውጤቱን ሲሞግቱ ባይደን የሽግግር ሥራ ጀምረዋል - ኖቬምበር 10, 2020
    ፕሬዚዳንት ትረምፕ በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊው ምርጫ ይጭበረበራል የሚለው እምነታቸውን አሁንም ገፍተውበታል፡፡ የአሜሪካ ድምጽ፣ የምርጫው አሸናፊ መሆናቸውን የተነበየው የቀድሞ ም/ል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ደግሞ በዚህ ሳምንት የኮቪድ-19 ግብረ ኃይል እንደሚያቋቁሙ አስታውቀዋል፡፡

    የባይደን የድል ንግግር፤ ስለምርጫው ውጤት የዓለም ምላሽ - ኖቬምበር 08, 2020

    የባይደን የድል ንግግር፤ ስለምርጫው ውጤት የዓለም ምላሽ - ኖቬምበር 08, 2020
    የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለአንድነትና ተከፋፍሎ የተራራቀውን የፖለቲካ አካሄድ ለማቀራረብ የሚጣራ ንግግር አድርገዋል። ተመራጩ ፕሬዚዳንት የድል ንግግራቸውን ያደረጉት የዘንድሮው ምርጫ ውጤት ወደ እርሣቸው ማጋደሉ ከተነገረ ከሰዓታት በኋላ ነበር።

    ኢትዮ ኤርትራዊያን ሴቶች ድምጻቸውን ከምን አኳያ ሰጡ? - ኖቬምበር 05, 2020

    ኢትዮ ኤርትራዊያን ሴቶች ድምጻቸውን ከምን አኳያ ሰጡ? - ኖቬምበር 05, 2020
    አርባ ስደስተኛው የአሜሪካ ምርጫ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀርቶታል፡፡ በዓለም ዙሪያ በጉጉት የሚጠበቀው ይሄ ምርጫ ለሁሉም ሰው የተለያየ ትርጉም አለው፡፡ በምርጫው የተሳተፉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኤርትራዊያን ሴቶች ለ46ኛው ፐሬዘዳንታዊ ምርጫ ድምጻቸውን በምን መመዘኛ ሰጡ? የአሜሪካ ድምጿ ኤደን ገረመው ታሰማናለች፡፡

    ትረምፕና ባይደን የመጨረሻውን የምርጫ ቅስቀሳ አካሄዱ - ኖቬምበር 03, 2020

    ትረምፕና ባይደን የመጨረሻውን የምርጫ ቅስቀሳ አካሄዱ - ኖቬምበር 03, 2020
    ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና ተፎካካሪያቸው የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የመጨረሻውን የምርጫ ዘመቻቸውን በተወሰኑ አሻሚ ግዛቶች የሚገኙ መራጮችን ድምጽ ለማግኘት ሲዘዋወሩ ከርመዋል፡፡ ይህን አስመልክቶ የቪኦኤው ዘጋቢ ብራየን ፓደን ዘገባ አዘጋጅቷል፡፡

    ሂስፓኒክ አሜሪካውያን በምርጫው ትልቅ ድርሻ ይኖራቸዋል - ኖቬምበር 03, 2020

    ሂስፓኒክ አሜሪካውያን በምርጫው ትልቅ ድርሻ ይኖራቸዋል - ኖቬምበር 03, 2020
    በ2020 ምርጫ፣ የሂስፓኒክ ማህበረሰብ አባላት፣ አብዛኛውን ቁጥር ካላቸው ነጭ አሜሪካውያን ቀጥለው ትልቁን የመራጮች ማህበረሰብ ቁጥር እንደሚይዙ ፒው የተባለው የምርምር ማዕክል አስታውቋል፡፡ የመጨረሻው ድምጽ ሊሰጥ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት በተሰበሰበው የኤን ቢሲ እና ዎል ስትሪት ጆርናል የህዝብ አስተያየት ድምጽ፣ በሂስፓኒክ መራጮች ዘንድ፣ የቀድሞ ምክትል ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ሁለት ለ አንድ በሆነ እጅ እንደሚበልጧቸው ተመልክቷል፡፡