የኢትዮጵያ ሚዲያ ተጨማሪ ፈተናዎች - ሜይ 11, 2022
በፖለቲካ፣ በአፋኝ ህጎች በመረጃ ማግኘት እና ከገቢ ጋር በተያያዙ ችግሮች ታጥሮ የኖረው የጋዜጠኝነት ሙያ ቀደም ሲል ከመንግስት ሲደርስበት ከቆየው ጫና በተጨማሪ ባልታወቁ ግለሰቦች እና ቡድኖች ለሚደርስ ጥቃት ተጋልጧል። ከማህበራዊ ሚዲያ መስፋፋት ጋር ተያይዞም ፈተናዎችም በርትተውበታል። በነዚህና ተያያዥ የኢትዮጵያ ሚዲያ ወቅታዊ ውጣ ውረዶች ዙሪያ በዩናይትድ ስቴትስ የሚሲሲፒ ዩንቨርስቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑትን ዶክተር ዘነበ በየነን አነጋግረናቸዋል።