Logo

    'ከሰኔ 30 በኋላ ምን ይመጣ ይሆን?' ዘላቂ መፍትሄ ያጣው የሃኪሞች ስራ አጥነት - ጁን 26, 2021

    amJune 25, 2021
    What was the main topic of the podcast episode?
    Summarise the key points discussed in the episode?
    Were there any notable quotes or insights from the speakers?
    Which popular books were mentioned in this episode?
    Were there any points particularly controversial or thought-provoking discussed in the episode?
    Were any current events or trending topics addressed in the episode?

    About this Episode

    ኢትዮጵያ እጅግ አነስተኛ የሆነ የጤና ባለሞያ ካለባቸው ሃገራት መሃከል ናት፡፡ ይሁንና በሃገሪቱ የህክምና ባለሞያዎች ስራ አጥ ናቸው፡፡ ከወራት በፊት በአማራ ክልል የሕክምና ባለሞያዎች የስራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን በዚህ መሰረትም የጤና ሚኒስቴር እና የክልሉ የጤና ቢሮ እስከ ሰኔ 30 ድረስ የሚቆይ የ3 ወራት የስራ እድል አመቻችተው ነበር፡፡ ይሁንና ከቀናት በሁላ የኮንትራት ጊዜያቸው ስለሚያልቅ የስራ አጥነት ስጋት ውስጥ ናገጥሟቸዋል፡፡

    Recent Episodes from ጤና - የአሜሪካ ድምፅ

    ራስን ማጥፋት የአይምሮ ጤና ቀውስ ውጤት ነው - ጃንዩወሪ 18, 2023

    ራስን ማጥፋት የአይምሮ ጤና ቀውስ ውጤት ነው  - ጃንዩወሪ 18, 2023
    ከቅርብ ግዜ ወዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎች ራሳቸውን ስለማጥፋታቸው በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በተደጋጋሚ ይሰማል። ማህበራዊ ሚዲያው ከቀደመው ጊዜ የበለጠ መረጃዎችን እንድንሰማ ማድረጉ እንዳለ ሆኖ፣ ራስን ማጥፋትን በተመለከተ ጥናት ያጠናው የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በየእለቱ 30 ሰዎች ራሳቸውን እንደሚያጠፉና በዚህም ምክንያት ቢያንስ 150 ሰዎች ቀሪ ህይወታቸውን የሚወዱት ሰው ራሱን በማጥፋቱ በሚያስከትለው መዘዝ ጥላ ስር እንደሚያሳልፉ አመልክቷል።

    አፍሪካ ሲዲሲ በአፍሪካ አራተኛው ዙር የኮቪድ ግርሻ አሳስቦኛል አለ - ዲሴምበር 24, 2021

    አፍሪካ ሲዲሲ በአፍሪካ አራተኛው ዙር የኮቪድ ግርሻ አሳስቦኛል አለ - ዲሴምበር 24, 2021
    የአፍሪካ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠሪያ ተቋም አፍሪካ ሲዲሲ አመት በዓል እየደረሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት በአህጉሪቱ እየተመዘገበ ያለው አዲሱ የኮቪድ 19 ስርጭት አሳስቦኛል አለ፡፡ የማዕከሉ ዳይሬክተር ጆን ንኬንጋሶንግ የአፍሪካ ሃገራት ክትባትን ላይ አስገዳጅ ደንብ እንዲያወጡ እየገፋን እንገኛለን ብለዋል፡፡

    አዲሱ የኮቪድ ዝርያ እና የዩናይትድ ስቴትስ ጥብቅ መመሪያ - ዲሴምበር 04, 2021

    አዲሱ የኮቪድ ዝርያ እና የዩናይትድ ስቴትስ ጥብቅ መመሪያ - ዲሴምበር 04, 2021
    ዩናይትድ ስቴትስ አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ኦሚኮርን በሃገሪቱ መገኘቱ ካረጋገጠች ከ24 ሰዓት በኋላ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ወደ ሃገሪቱ የሚገቡ ዓለም አቀፍ ተጓዦችን በተመለከተ ጥብቅ መመሪያዎችን ያወጡ ሲሆን በሃመላው ሃገሪቱ በመጓጓዣዎች ላይ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል መመሪያዎችም ለተራዘመ ጊዜ እንዲቆዩ አድርገዋል፡፡ ፕሬዘዳንቱ በተጨማሪም 200 ሚሊየን የኮቪድ 19 ክትባቶች በቀጣይ ወር ለሌሎች ሃገራት እንደሚለገሱም ቃል ገብተዋል፡፡

    የጽንስ ማቋረጥ እሰጥ አገባ በዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ፍ/ቤት - ዲሴምበር 02, 2021

    የጽንስ ማቋረጥ እሰጥ አገባ በዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ፍ/ቤት - ዲሴምበር 02, 2021
    በትላንትናው ዕለት የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጽንስ ማቋረጥን በሚደግፍ የግዛት ሕግ ዙሪያ ክርክሮችን የሰማ ሲሆን፤ በጽንስ ማቋረጥ ዙሪያ ለብዙ አስርት ዓመታት የዘለቀውን ክርክር ተከትሎ የተቃውሞ ድምጾች ሲስተጋቡ ውለዋል፡፡

    የ2021 የዓለም አቀፍ የፊጎ አዋርድ ተሸላሚ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ማናቸው? - ኖቬምበር 01, 2021

    የ2021 የዓለም አቀፍ የፊጎ አዋርድ ተሸላሚ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ማናቸው? - ኖቬምበር 01, 2021
    ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር መቅደስ ዳባ በቅዱስ ፓውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የማህጸን እና የጽንስ ህክምና ሃኪም እንዲሁም በኢትዮጵያ  የጽንስ እና የማሕጸን ሃኪሞች ማህበር ፕሬዘዳንት ናቸው፡፡ በቅርቡም ዓለም አቀፍ የጽንስ እና የማህጸን ፌደሬሽን በአለም ዙሪያ በዘርፉ በምርመር አስተዋጽኦ አድርገዋል በሚል የጎርጎሮሳዊያኑ 2021 ዓ.ም ከመረጣቸው ባለሞያዎች መሃከል አንዷ በመሆን የፊጎ አዋርድ/ሽልማት ወስደዋል፡፡

    የህፃናትን ስነ-ባህሪና እድገት የሚያጠናው የመጀመሪያው ተቋም - ኦክቶበር 07, 2021

    የህፃናትን ስነ-ባህሪና እድገት የሚያጠናው የመጀመሪያው ተቋም - ኦክቶበር 07, 2021
    ጎጆ የህሙማን መጠለያ ተቋምን በመመስረት በሺዎች ለሚቆጠሩ አቅመ ደካማ ህሙማን ድጋፍ እየሰጠች የምትገኘው ዶክተር ሰላሜነሽ ፅጌ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የህፃናት ስነ-ባህሪና የእድገት ሁኔታን የሚያጠና ተቋም በጥቁር አምበሳ ሆስፒታል ስር እንዲጀመር ያደረገች የህፃናት ሀኪም ናት።

    የአዲስ አበባ መምህራን ስራ ከመጀምራቸው በፊት እንዲከተቡ ስለሚያደርገው መመሪያ ምን ይላሉ? - ኦክቶበር 02, 2021

    የአዲስ አበባ መምህራን ስራ ከመጀምራቸው በፊት እንዲከተቡ ስለሚያደርገው መመሪያ ምን ይላሉ? - ኦክቶበር 02, 2021
    ጥቅምት 1 ትምህርት ከመጀመሩ በፊት የአ.አ ትምህርት ቢሮ መምህራን እና የትምህርት ቤት አስተዳደር አባላት ከስራቸው አንጻር ከፍተኛ የሆነ የኮቪድ 19 ተጋላጭነት እንዳላቸው በመገንዘብ እራሳቸውንም ሆነ ቤተሰባቸውን ከበሽታው እንዲጠብቁ ለማስቻል አስገዳጅ የሆነ የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት እንዲወስዱ አስገዳጅ የሆነ መመሪያ ወጥቷል፡፡ በዚህ ጉዳይ ምምህራኑ ምን ይላሉ?

    ለተቸገሩ ህሙማን እና አስታማሚዎች ማረፊያ የሆነችው ሀኪም - ሴፕቴምበር 03, 2021

    ለተቸገሩ ህሙማን እና አስታማሚዎች ማረፊያ የሆነችው ሀኪም - ሴፕቴምበር 03, 2021
    አሜሪካ በየአመቱ ለአፍሪካ ወጣት መሪዎች በምታዘጋጀው የማንዴላ ፌሎውሺፕ በዚህ አመት ከኢትዮጵያ ከተመረጡት መሀከል ጎጆ የህሙማን መጠለያ ተቋምን የመሰረተችው ዶክተር ሰላሜነሽ ፅጌ አንዷ ናት። ተቋሙ ከኢትዮጵያ የገጠር ከተሞች ለተጨማሪ ህክምና አዲስ አበባ የሚመጡ፣ ማረፊያ በማጣትና ገንዘባቸውን ለህክምና በመጨረስ ለጎዳና ህይወት የሚዳረጉ ህሙማንን በጊዜያዊነት የሚያስጠልል ሲሆን ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ ከ81 ሺህ በላይ የሚሆኑ ህሙማን ረድቷል።

    'የአማኑኤል ሆስፒታል ታሪኮች' ቆይታ ከአእምሮ ሃኪሙ ዶ/ር ዮናስ ላቀው ጋር - ሴፕቴምበር 01, 2021

    'የአማኑኤል ሆስፒታል ታሪኮች' ቆይታ ከአእምሮ ሃኪሙ ዶ/ር ዮናስ ላቀው ጋር - ሴፕቴምበር 01, 2021
    ብዙ ሰዎች በአማኑኤል የአእምሮ ሆስፒታል ታክመው ከዳኑ በኋላ እዛ መታከማቸውን መናገር ይፈራሉ ይላል ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ድንገት እነዚህ ሰዎች ከሰው ለየት ያለ ነገር ሲናገሩም ሆነ ሲሰሩ ቢታዩ “እሱ/ እሷ ድሮስ ከአማኑኤል አይደል እንዴ የመጡት?” ይባላሉ ይላል ዶ/ር ዮናስ ላቀው፡፡ እንደውም ከነጭራሹም እዛ የምትሰሩት እራሳቹ ‘እብዶች አይደላቹ እንዴ?’ ተብዬም አውቃለሁ ይላል፡፡ ሙሉውን ቃለምልልስ ያድምጡት፡፡