Logo

    ኢትዮጵያዊያን በአሜሪካ - የአሜሪካ ድምፅ

    የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡
    am50 Episodes

    People also ask

    What is the main theme of the podcast?
    Who are some of the popular guests the podcast?
    Were there any controversial topics discussed in the podcast?
    Were any current trending topics addressed in the podcast?
    What popular books were mentioned in the podcast?

    Episodes (50)

    ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ዐይን የቃኘ መጽሃፍ ለንባብ በቃ - ኦክቶበር 11, 2023

    ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ዐይን የቃኘ መጽሃፍ ለንባብ በቃ - ኦክቶበር 11, 2023
    "Unleashing Diplomatic Dynamo: Ethiopia Unbound-Western Loss, China's Rise " ፣ በቀድሞው ዲፕሎማት ዘነበ ኃይለማሪያም ገነሜ ተጽፎ በቅርቡ ለአንባቢያን የቀረበ መጽሐፍ ነው። በዳላስ ቴክሳስ በንግድ አማካሪነት የሚሰሩት ጸሓፊው ፣የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ገጽታ፣ የዲያስፖራውን ሚና፣ ከምዕራቡ ዓለም ጋር ያላትን ግንኙነት እና ሌሎች ጉዳዮችን በወፍ በረር ቃኝተዋል ። ሀብታሙ ስዩም በመጽሃፉ ዙሪያ አነጋግሯቸዋል ።

    'ትግራይ መጠበቅ አትችልም' የድረገጽ የሰብዓዊ ድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ተካሄደ - ኦገስት 14, 2021

    'ትግራይ መጠበቅ አትችልም' የድረገጽ የሰብዓዊ ድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ተካሄደ - ኦገስት 14, 2021
    ትግራይ ካንት ዌይት ወይም ‘ትግራይ መጠበቅ አትችልም’ ሲሉ ነዋሪነታቸውን በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ ያደረጉ የትግራይ ምሁራን እና ተወላጆች በትላንትናው ዕለት በዋሽንግተን ሰዓት አቆጣጠር ከእኩለ ቀን እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ክለብ ሃውስ በተሰኘ የውይይት መተግበሪያ ላይ በመገናኘት ጥናታዊ ጽሆፎችን በማቅረብ፣ በጎ ፈንድ ሚ እና በሌሎች የገንዘብ ማሰባሰቢያ መንገዶች በመጠቀም የገቢ ማሰባሰቢያ አድርገዋል፡፡

    የሃያ ዓመታት የትግል ጉዞ እና ስኬት- ዋስ ምጣድ - ዲሴምበር 09, 2020

    የሃያ ዓመታት የትግል ጉዞ እና ስኬት- ዋስ ምጣድ - ዲሴምበር 09, 2020
    ዋሴ ሙሉጌታ የዋስ ምጣድ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ነው፡፡ ዋስ ምጣድ በኢትዮጵያ፣ በሰሜን አሜሪካ፣ በካናዳ፣ በስዊድን እና በጀርመን ሃገር የሚሽጥ ሲሆን ከመደበኛው ምጣድ በሶስት እጅ ያነሰ ሃይል እንደሚጠቀምም ዋሴ ይናገራል፡፡ በዓመት ከአንድ ሚሊየን ዶላር በላይ የንግድ ሽያጭ ያለው የዋስ ምጣድ በአሁን ሰዓት በደብረብርሃን ከተማ የማምረቻ ፍቃድ ወስዶ ፋብሪካ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ ኤደን ገረመው ከዋሴ ሙልጌታ ጋር የነበራትን ቆይታ በተከታዩ ዘገባ ታሰማናለች፡፡

    ኢትዮጵያዊው የማር ወይን ነጋዴ የ750 ሺህ ዶላር አሸናፊ ሆነ - ዲሴምበር 05, 2020

    ኢትዮጵያዊው የማር ወይን ነጋዴ የ750 ሺህ ዶላር አሸናፊ ሆነ - ዲሴምበር 05, 2020
    በካሊፎርኒያ ሶኖማ ግዛት የሚኖረው አየለ ሰለሞን የጠጅ ባህል በማጥናት የጠጅ ጣዕም እና ሽታ ያለው የማር ወይን መጥመቅ ችሏል፡፡ ላለፉት አምስት ዓመታትም ቢ ዲቫይን የተሰኘውን የማር ጠጅ በመሸጥ እና በዓለም ዙሪያ በማስተዋወቅ ላይ ቆይቷል፡፡ የኮቪድ 19 ወረሽኝ ከፍተኛ ወደሆነ ኪሳራ እና የገበያ መቀስዛቀዝ ያደረሰበት ሲሆን ይህን ችግሩን ለመቅረፍም በአሜሪካ ግዙፉ በሆነው የንግድ ውድድር ሻርክ ታንክ ውስጥ በምሳተፍ 750,000 ዶላር አሸናፊ ሆኗል፡፡

    የኦስቲን ከተማን የ150 ዓመት ታሪክ የቀየረው ትውልደ -ኢትዮጵያዊ - ኖቬምበር 10, 2020

    የኦስቲን ከተማን የ150 ዓመት ታሪክ የቀየረው ትውልደ -ኢትዮጵያዊ - ኖቬምበር 10, 2020
    ኦባላ ኦባላ በሜኔሶታ ግዛት -ኦስቲን ከተማ ምክር ቤት አባል ለመሆን ተወዳድሮ ያሸነፈ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ነው። ገና የአሜሪካ ዜግነቱን ባገኘ በዓመቱ ለዚህ ድል የበቃው የ27 ዓመቱ ወጣት እዚህ ከመድረሱ በፊት ብዙ ውጣውረዶችን አይቷል። በኦስቲን ግዛት ታሪክ ለየት ያለው ድሉ ለብዙ ስደተኞች ተስፋን እንደሚፈነጥቅም ይናገራል። ከኦስቲን ከተማ ምክር ቤት አባል ኦባላ ኦባላ ጋር አጭር ቆይታ ያደረገው ሀብታሙ ስዩም ቀጣዩን ዘገባ አሰናድቷል።

    የፒፕል ቱ ፒፕል ኮንፈረንስና እውቅና የተሰጣቸው ኢትዮጵያውያን - ኦክቶበር 21, 2020

    የፒፕል ቱ ፒፕል ኮንፈረንስና እውቅና የተሰጣቸው ኢትዮጵያውያን - ኦክቶበር 21, 2020
    በመላው ዓለም የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችን በማስተባበር የኢትዮጵያን ጤና ዘርፍ ችግሮች ለመቅረፍና የሚደረጉ ጥረቶችን ለማገዝ የተቋቋመው የፒፕል ቱ ፒፕል ድርጅት፣ 14ኛውን ዓመታዊ ኮንፈረንስ አካሂዷል፡፡ በድረ ገጽ ላይ በተካሄደው በዚህ የፒፕል ቱ ፒፕል ዝግጅት፣ የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን ጨምሮ በርካታ እንግዶችና እውቅ የጤና ባለሙያዎች ኮቪድ 19ን ጨምሮ በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ላይ ሙያዊ ንግግር አሰምተዋል፡፡

    የዩናትድ ስቴትስ ቆጠራና ኢትዮጵያውያን - ኦገስት 16, 2020

    የዩናትድ ስቴትስ ቆጠራና ኢትዮጵያውያን - ኦገስት 16, 2020
    በዩናይትድ ስቴትስ በየአሥር ዓመቱ አንዴ የሚደረገው የህዝብ ቆጠራ ዘንድሮም ይካሄዳል።፡ የቆጠራው መጠናቀቂያ ጊዜ ከኅዳር ወደ መስከረም እንዲያጥር በመደረጉ ሊጠናቀቅ የቀሩት ከሁለት ወራት ያነሰ ጊዜ ነው። የኢትዮጵያውያን ተሳትፎ ምን ይመስላል?

    ኢትዮጵያዊው ገብረእግዚአብሔር ገብረ ለሃርማን ጄምነር ሽልማት እጩ ሆነ - ጁላይ 16, 2020

    ኢትዮጵያዊው ገብረእግዚአብሔር ገብረ ለሃርማን ጄምነር ሽልማት እጩ ሆነ - ጁላይ 16, 2020
    በ1977 ድርቅ ወላጆቹን ያጣው ገ/እግዚአብሔር ገብረ በመቀሌ ኤስ.ኦ.ኤስ የሕጻናት መንደር ውስጥ ነው ያደገው፡፡ የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ምሩቅ ሲሆን የኢትዮጵያ ህጻናት እንዲማሩ ለሚያደርገው አበርክቶት ለሽልማት እጩ ሆኗል፡፡ ቆይታውን ያዳምጡ፡፡

    ሁለት የንግድ ቤታቸውን በቃጥሎ ያጡት ቤተሰቦች - ጁን 13, 2020

    ሁለት የንግድ ቤታቸውን በቃጥሎ ያጡት ቤተሰቦች - ጁን 13, 2020
    የአፍሪካ አሜሪካዊውን ጆርጅ ፍሎይድ ኢ- ሰብዓዊ አሟሟት ተከተሎ በተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ በተነሱ ግጭቶች ሳቢያ በአሜሪካን ሃገር ሚኒሶታ ግዛት ሜኒያፖሊስ ከተማ ነዋሪ የሆኑት የቦሌ ሬስቶራንት ባለቤቶች ሁለት የንግድ ቤቶቻቸውን በቃጠሎ አጥተዋል፡፡ ይሁን እንጂ "ምንም እንኳን የዘመናት የላባችን ውጤት በመውደሙ ሃዘን ቢሰማንም በምንም ዓይነት ግን ከሰው ሕይወት ጋር አይወዳደርም" ይላሉ፡፡ ከአሜሪካ ድምጿ ኤደን ገረመው ጋር የነበራቸውን ቆይታ ይከታተሉ፡፡

    በኮቪድ-19 ዙሪያ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞችን ለማብቃት በሰሜን አሜሪካ ያሉ ሃኪሞች ጥረት - ኤፕሪል 20, 2020

    በኮቪድ-19 ዙሪያ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞችን ለማብቃት በሰሜን አሜሪካ ያሉ ሃኪሞች ጥረት - ኤፕሪል 20, 2020
    በአሜሪካን አገር በተለያዩ ግዛቶች የሚኖሩ ሰባት የሕክምና ባለሙያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኮቪድ19ን ስርጭት ለመከላከል እና ድጋፍ ለማድረግ በሚል YGT በሚል ስያሜ ስለ ኮቪድ19 ለሕክምና ባለሞያዎች እና በተለያዩ የገጠር ከተሞች ለሚገኙ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች በቪዲዮ የሚቀርቡ ትምህርቶች(ዊብናር)አዘጋጅተዋል፡፡ የቡድኑ አባል እና በካሊፎርኒያ ሳንዋኪን ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ታፈረ ንጋት ስለቡድኑ ለአሜሪካ ድምጽ አስረድተዋል፡፡

    የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ አምስት ፕሮጀክቶችን ለመጨረሻው ዙር አሳለፈ፡፡ - ፌብሩወሪ 11, 2020

    የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ አምስት ፕሮጀክቶችን ለመጨረሻው ዙር አሳለፈ፡፡ - ፌብሩወሪ 11, 2020
    የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ለመጨረሻ ዙር ካቀረባቸው 22 እጩ ፕሮጅክቶች አምስቱን መምረጡን እና ተፈራርሞ ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅቱን እየጨረሰ መሆኑን ከሰሞኑ አስታውቆዋል፡፡ የዲያስፖራ ትረስት ፈንዱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወ/ሮ ሃና አጥናፉ ስለተመረጡት ፕሮጀክቶች ይዘት እና ስለአጠቃላይ ሁኔታው ከኤደን ገረመው ጋር ተነጋገረው ነበረ፡፡

    ዓለም የኮቢ ብራያንትን ህልፈት በሃዘን እያስታወሰ ነው - ጃንዩወሪ 30, 2020

    ዓለም የኮቢ ብራያንትን ህልፈት በሃዘን እያስታወሰ ነው - ጃንዩወሪ 30, 2020
    በሄሊኮፕተር መከስከስ አደጋ ህይወቱ ያለፈው ታላቁ የቅርጫት ኳስ ኮከብ ኮቢ ብራያንትን ዓለም በሃዘን እያስታወሰ ነው። የሎስ አንጀለስ ከተማ ይህ ክፉ ዜና ከተሰማበት ጊዜ አንስቶ ለታላቁ የስፖርት ሰው ያለውን ክብር በህልፈቱ የተሰማውን ሃዘን እየገለጸ ነው።
    Logo

    © 2024 Podcastworld. All rights reserved

    Stay up to date

    For any inquiries, please email us at hello@podcastworld.io