ኢትዮጵያ 100 ግድቦችን እገነባለሁ ማለቷ ግብፅን አስቆጥቷል - ጁን 03, 2021
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ በመጪው አመት እስከ 100 የሚደርሱ አነስተኛና መሀከለኛ ግድቦችን እገነባለሁ ማለታቸውን ተቃውመው የግብፅ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ትላንት መግለጫ አውጥተዋል። የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ህጎችን እስካከበረች ድረስ የተፈጥሮ ሀብቷን መጠቀም ትችላለች ማለታቸውን ፋና ብሮድካቲንግ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።